Home » Music » Amharic worship -Egziabher kenie gar

Amharic worship -Egziabher kenie gar

Written By Eyesus Tube on Saturday, Jun 15, 2013 | 03:00 PM

 
እግዚኣብሄር ከኔ ጋር ባይሆን ኖሮ በነዚህ ኣመታት በክንዱ ደግፎ ባያሻግረኝ ክፉዎቹ ቀናት ኣጠገቤ ቆሞ ባያበረታኝ በነውጡ ሰኣት ህያው ሳለሁኝ በዋጠኝ ነበር ጠላቴ እንደቁጣው ጽናት /2/ የኣመጻን ፈሳሽ ያደረቀው የጥፋትን እንባ የገደበው ነፍሴን እንደወፍ ከኣዳኞች ወጥመድ ያስመለጣት ላኖረኝ ጌታዬ እስቲ ልሰዋ የምስጋናን መስዋእት ሃሌሉያ..... በመከራዬ ቀን ልመናዬን ሰማ ከላይ ከመቅደሱ ረድኤትን ላከልኝ የጠላቶቼን/የከሳሾቼን/ ከፍታ ኣስረገጠኝ በማዳኑ እጅግ ደስ ኣሰኘኝ /2/ ሃሌሉያ..... ለጥርሱ ንክሻ ያላደረገኝ ከተደበቀብኝ ወጥመድ ኣዳነኝ ነፍሴን ከመከራ ሁሉ ላዳናት ለጌታ ለየሱስ ዛሬም ልገዛለት ሃሌሉያ..... ምንም ያህል ብዙ ወዳጆች ቢኖሩኝ በመከራ ቀን ግን ማንም ኣይገኝም እሱ ሳይለወጥ/ፊቱ ሳይቀየር/ ልመናን ሚፈጽም ታማኙ እግዚኣብሄር ይክበር ለዘላለም /2/ ሃሌሉያ...... የተግሳጽና የዘለፋው ብዛት ኣቤት በመከራ ቀን የተግዳሮት ኣይነት የጠላትን ትእቢት የጨለማው ብርታት በኣንዲት/በኣፉ/ ቃል ሽሮ ያከብራል በድንገት /በቅጽበት/ /2/ /ኣዝ/ እግዚኣብሄር ከኔ ጋር ባይሆን ኖሮ.............