Home » Travel & Events » Waldba on ESAT radio Feb 1

Waldba on ESAT radio Feb 1

Written By Save Waldba on Saturday, Feb 02, 2013 | 03:48 PM

 
ዋልድባ ገዳም ዛሬም እንግልት፣ እስራት፣ ድብደባ በክልሉ ባለሥልጣናት (ባለጊዜዎች) እየደረሰ ነው። መነኮሳት ለሃገር እና ለወገን ከሚጸልዩበት ከትግራይ ክልል ውጡ አማርኛ ተናጋሪዎች ናችሁ ተብለው በግፍ ተባረው በተለያዩ የአማራ ክልል ከተሞች እየተንከራተቱ እና እየተጉላሉ ነው። የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች ትልቅ ተጋድሎ እያደረጉ ቢሆንም እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ቤተክርስቲያችን፣ ሃይማኖታችንን ከእኛ በላይ ሊጠብቃት የሚችል እንደሌለ አምኖ ቤተክርስቲያኑን እና ሃይማኖቱን ከግብረ በላ ባለጊዜዎች ሊጠብቅ ቀናያን አባቶቹን ሊጠብቅ እና ሊንከባከብ ይገባል ብለን እናምናለን ዋልድባን እንታደግ